መዝሙር 16:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።

7. የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።

8. እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

9. ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤

10. በሲኦል ውስጥ አትተወኝምና፤ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።

11. የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

መዝሙር 16