መዝሙር 15:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ጽድቅን የሚያደርግ፤ከልቡ እውነትን የሚናገር፤

3. በምላሱ የማይሸነግል፤በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ወዳጁን የማያማ፤

4. ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤

5. ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣በንጹሓን ላይ ጒቦ የማይቀበል፤እነዚህን የሚያደርግ፣ከቶ አይናወጥም።

መዝሙር 15