መዝሙር 147:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ።አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው፤እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።

2. እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።

3. ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ቍስላቸውንም ይጠግናል።

4. የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።

መዝሙር 147