መዝሙር 146:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።

5. ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤

6. እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤

መዝሙር 146