መዝሙር 144:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።

6. የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ፍላጻህን ሰደህ ግራ አጋባቸው።

7. እጅህን ከላይ ዘርጋ፤ከኀይለኛ ውሃ፣ከባዕዳንም እጅ፣ታደገኝ፤ አድነኝም፤

8. አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።

9. አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።

10. ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።

መዝሙር 144