3. ጠላት እስከ ሞት አሳዶኛል፤ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሎአል፤ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።
4. ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ልቤም በውስጤ ደንግጦአል።
5. የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ።
6. እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ
7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤መንፈሴ ደከመች፤ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ፊትህን ከእኔ አትሰውር።
8. በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።