መዝሙር 143:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ልመናዬን አድምጥ፤በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ሰምተህ መልስልኝ።

2. ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው።

3. ጠላት እስከ ሞት አሳዶኛል፤ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሎአል፤ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።

4. ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ልቤም በውስጤ ደንግጦአል።

5. የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ።

መዝሙር 143