መዝሙር 136:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

8. ፀሓይ በቀን እንዲሠለጥን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

9. ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

10. የግብፅን በኵር የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

11. እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

መዝሙር 136