መዝሙር 135:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም ወድሱ፤እናንት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤

2. በእግዚአብሔር ቤት፣በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።

3. እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤

4. እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።

መዝሙር 135