መዝሙር 132:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. “ወደ ቤቴ አልገባም፤ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤

4. ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤

5. ለእግዚአብሔር ስፍራን፣ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”

6. እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤በቂርያትይዓሪም አገኘነው።

7. “ወደ ማደሪያው እንግባ፤እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።

መዝሙር 132