መዝሙር 129:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል እንዲህ ይበል፦“ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤

2. በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም።

3. ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ትልማቸውንም አስረዘሙት።”

4. እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።

መዝሙር 129