መዝሙር 122:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል።

6. እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤“የሚወዱሽ ይለምልሙ፤

7. በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”።

8. ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ፣“በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።

9. ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት፣በጎነትሽን እሻለሁ።

መዝሙር 122