መዝሙር 121:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤የሚጠብቅህም አይተኛም።

4. እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።

5. እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።

6. ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አታመጣብህም።

መዝሙር 121