መዝሙር 12:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ።

8. በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።

መዝሙር 12