መዝሙር 119:99-104 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

99. ምስክርነትህን አሰላስላለሁና፣ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የላቀ አስተዋይ ልብ አገኘሁ።

100. መመሪያህን ተከትዬ እሄዳለሁና፣ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋይ ሆንሁ።

101. ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣እግሬን ከክፉ መንገድ ሁሉ ከለከልሁ።

102. አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና፣ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም።

103. ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው!ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው።

104. ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

መዝሙር 119