መዝሙር 119:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ፤ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።

20. ዘወትር ደንብህን በመናፈቅ፣ነፍሴ እጅግ ዛለች።

21. ከትእዛዛትህ የሳቱትን፣እብሪተኞችንና ርጉሞችን ትገሥጻለህ።

22. ምስክርነትህን ጠብቄአለሁና፣ስድብንና ንቀትን ከእኔ አርቅ።

23. ገዦች ተቀምጠው ቢዶልቱብኝ እንኳ፣አገልጋይህ ሥርዐትህን ያሰላስላል።

መዝሙር 119