መዝሙር 119:164-167 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

164. ጻድቅ ስለ ሆነው ሕግህ፤በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ።

165. ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ዕንቅፋትም የለባቸውም።

166. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ትእዛዝህንም እፈጽማለሁ።

167. ነፍሴ ምስክርነትህን ትጠብቃለች፤እጅግ እወደዋለሁና።

መዝሙር 119