መዝሙር 119:161-165 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

161. ገዦች ያለ ምክንያት አሳደዱኝ፤ልቤ ግን ከቃልህ የተነሣ እጅግ ፈራ።

162. ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፤በቃልህ ደስ አለኝ።

163. ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

164. ጻድቅ ስለ ሆነው ሕግህ፤በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ።

165. ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ዕንቅፋትም የለባቸውም።

መዝሙር 119