መዝሙር 119:111-115 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

111. ምስክርነትህ የዘላለም ውርሴ ናት፤ልቤ በዚህ ሐሤት ያደርጋልና።

112. ትእዛዝህን ለዘላለም፣ እስከ ወዲያኛው ለመፈጸም፣ልቤን ወደዚያው አዘነበልሁ።

113. መንታ ልብ ያላቸውን ጠላሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

114. አንተ መጠጊያዬና ጋሻዬ ነህ፤ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ።

115. የአምላኬን ትእዛዛት እጠብቅ ዘንድ፣እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ ከእኔ ራቁ።

መዝሙር 119