መዝሙር 118:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ።

18. መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።

19. የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

20. ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ጻድቃን በእርሷ በኩል ይገባሉ።

መዝሙር 118