1. እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑት፤ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
2. የእስራኤል ሕዝብ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።
3. የአሮን ቤት፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።
4. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣“ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።
5. በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።
6. እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?