መዝሙር 115:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

12. እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንንም ቤት ይባርካል።

13. እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ፣ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።

14. እግዚአብሔር እናንተንና ልጆቻችሁን፣በባርኮቱ ያብዛችሁ።

መዝሙር 115