መዝሙር 113:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?

6. በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?

7. ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

8. ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።

9. መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።ሃሌ ሉያ።

መዝሙር 113