መዝሙር 110:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሎአል፤እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

5. ጌታ በቀኝህ ነው፤በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቃቸዋል።

6. በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል።

7. መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል።

መዝሙር 110