መዝሙር 109:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው።

20. እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን።

21. አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ።

22. እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ልቤም በውስጤ ቈስሎአልና።

መዝሙር 109