መዝሙር 109:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።

11. ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።

12. ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

13. ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

14. የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።

መዝሙር 109