መዝሙር 107:41-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ችግረኞችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።

42. ልበ ቅኖች ይህን አይተው ሐሤት ያደርጋሉ፤ጥመትም ሁሉ አፏን ትዘጋለች።

43. እንግዲህ ማንም ብልህ ቢሆን፣ ይህን ነገር ልብ ይበል፤እርሱም የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል።

መዝሙር 107