መዝሙር 107:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

16. እርሱ የናሱን በሮች ሰብሮአልና፤የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጦአል።

17. አንዳንዶቹ ከዐመፃቸው የተነሣ ቂሎች ሆኑ፤ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ገቡ።

18. ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።

19. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

መዝሙር 107