መዝሙር 106:25-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጒረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም።

26. በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣እጁን አንሥቶ ማለ፤

27. ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ።

28. ራሳቸውን ከብዔል ፌጎር ጋር አቈራኙ፤ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤

29. በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ቸነፈርም በላያቸው መጣ።

30. ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ቸነፈሩም ተገታ፤

31. ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።

32. ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤

33. የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።

34. እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት፣ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኋላ አሉ፤

35. እንዲያውም ከሕዝቦቹ ጋር ተደባለቁ፤ልማዳቸውንም ቀሠሙ፤

36. ጣዖቶቻቸውንም አመለኩ፤ይህም ወጥመድ ሆነባቸው።

37. ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንለአጋንንት ሠዉ።

38. የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ምድሪቱም በደም ተበከለች።

መዝሙር 106