መዝሙር 106:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።

2. ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል?ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?

3. ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ጽድቅን ሁል ጊዜ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤

5. ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው።

መዝሙር 106