መዝሙር 105:41-45 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለደለ፤እንደ ወንዝም በበረሓ ፈሰሰ።

42. ለባሪያው ለአብርሃም የሰጠውን፣ቅዱስ የተስፋ ቃሉን አስቦአልና።

43. ሕዝቡን በደስታ፣ምርጦቹንም በእልልታ አወጣቸው።

44. የሌሎችን ሕዝቦች ምድር ሰጣቸው፤የእነዚህንም የድካም ፍሬ ወረሱ፤

45. ይህም ሥርዐቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ሕጉንም ይፈጽሙ ዘንድ ነው።ሃሌ ሉያ።

መዝሙር 105