መዝሙር 105:25-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ሕዝቡን እንዲጠሉ፣በባሪያዎቹም ላይ እንዲያሤሩ ልባቸውን ለወጠ።

26. ባሪያውን ሙሴን፣የመረጠውንም አሮንን ላከ።

27. እነርሱም ታምራታዊ ምልክቶችን በመካከላቸው፣ድንቅ ነገሮቹንም በካም ምድር አደረጉ።

28. ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ።

29. ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሦቻቸውንም ፈጀ።

30. ምድራቸውም፣ የነገሥታታቸው እልፍኝ ሳይቀር፣ጓጒንቸር ተርመሰመሰባቸው።

31. እርሱ በተናገረ ጊዜ የዝንብ መንጋ መጣ፤ትንኞችም ምድራቸውን ወረሩ።

32. ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፤ምድራቸውም ሁሉ መብረቅ አወረደ።

33. ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፤የአገራቸውንም ዛፍ ከተከተ።

34. እርሱ በተናገረ ጊዜ አንበጣ መጣ፤ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ ከተፍ አለ፤

35. የምድሪቱንም ዕፀዋት ሁሉ በላ፤የመሬታቸውንም ፍሬ ሙጥጥ አደረገ፤

36. ደግሞም በአገራቸው ያለውን በኵር ሁሉ፣የኀይላቸውንም ሁሉ በኵራት መታ።

መዝሙር 105