መዝሙር 103:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. መንገዱን ለሙሴ፣ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።

8. እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።

9. እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ለዘላለምም አይቈጣም።

10. እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

11. ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።

መዝሙር 103