መዝሙር 103:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣

4. ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣

5. ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።

6. እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።

መዝሙር 103