መዝሙር 103:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪየውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ።

2. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤

3. ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣

4. ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣

መዝሙር 103