መዝሙር 10:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ?በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?

2. ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።

3. ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።

4. ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤

5. መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው።በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።

መዝሙር 10