መክብብ 9:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

13. እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፦

14. ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት።

መክብብ 9