መክብብ 8:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በእግዚአብሔር ፊት መሐላ ስለፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ።

3. ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ።

4. የንጉሥ ቃል የበላይ ስለ ሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል?

5. እርሱን የሚታዘዝ ሁሉ አይጐዳም፤ጥበበኛም ልብ ትክክለኛውን ጊዜና ተገቢውን አሠራር ያውቃል።

6. የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው።

7. ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?

መክብብ 8