መክብብ 7:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል፤ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል።

2. ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ፣ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤ሞት የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፤ሕያው የሆነም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል።

3. ሐዘን ከሣቅ ይሻላል፤ያዘነ ፊት ለልብ መልካም ነውና።

4. የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።

መክብብ 7