4. እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
5. ሰነፍ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል።
6. በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።
7. ደግሞም ከፀሓይ በታች ከንቱ የሆነን ነገር አየሁ፤
8. ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ብቸኛ ሰው አለ፤ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው?ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበውለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።
9. ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤
10. አንዱ ቢወድቅ፣ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል።ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣እንዴት አሳዛኝ ነው!