መክብብ 2:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ዐይኔ የፈለገውን ሁሉ አልከለከልሁትም፤ለልቤም ምድራዊ ደስታን አልነፈግሁትም፤ልቤ በሠራሁት ሁሉ ደስ አለው፤ይህም የድካሜ ሁሉ ዋጋ ነበረ።

11. ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።

12. ከዚያም ጥበብን፣እብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ሐሳቤን መለስሁ፤አስቀድሞ ከተደረገው በቀር፣ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል?

13. ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ ሁሉ፣ጥበብም ከሞኝነት እንደሚበልጥ ተመለከትሁ።

መክብብ 2