ሕዝቅኤል 42:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በሩ በሰሜን ትይዩ የሆነው ሕንጻ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ወርዱም አምሳ ክንድ ነበር።

3. ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ።

4. ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ።

ሕዝቅኤል 42