1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አዙር፤ ትንቢትም ተናገርበት፤
3. እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሴይር ተራራ ሆይ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ጠፍ አደርግሃለሁ።
4. ከተሞችህን ፍርስራሽ አደርጋቸዋለሁ፤ ባድማ ትሆናለህ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ።
5. “ ‘እስራኤላውያን ቅጣታቸው እጅግ መራራ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ፍዳቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ የጥንቱን ቂም ቋጥረህ ለሰይፍ ስለ ዳረግሃቸው፤