11. ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ሰይፋቸውን በግብፅ ላይ ይመዛሉ፤ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
12. የዐባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
13. “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤በሜምፊስ ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ።ከእንግዲህ በግብፅ ገዥ አይኖርም፣በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
14. ጳፕሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤በቴብስ ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
15. የግብፅ ምሽግ በሆነችው፣በሲን ላይ መዓቴን አፈሳለሁ፤ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።