ሕዝቅኤል 30:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤“ወዮ ለዚያ ቀን!”

3. ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤የደመና ቀን፣ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።

4. በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ይወሰዳል፤መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።

ሕዝቅኤል 30