8. ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።
9. ልምድ ያካበቱ የጌባል ባለ ሙያዎች፣መርከብሽን ለመገጣጠም በመካከልሽ ነበሩ፤የባሕር መርከቦችና መርከበኞቻቸው ሁሉ፣ከአንቺ ጋር ሊገበያዩ ይመጡ ነበር።
10. “ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥአገለገሉ፤ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።
11. የአራድና የሔሌክ ሰዎች፣ቅጥርሽን በየአቅጣጫው ጠበቁ፤የገማድ ሰዎችም፣ በምሽግሽ ውስጥ ነበሩ።ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።
12. “ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።
13. “ ‘ያዋን፣ ቶቤልና ሞሳሕ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር፤ ባሪያዎችንና የናስ ዕቃዎችን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
14. “ ‘የቤት ቴርጋማ ሰዎችም መጋዣዎችን፣ የጦር ፈረሶችንና በቅሎዎችን በሸቀጥሽ ለወጡ።
15. “ ‘የድዳን ሰዎች ከአንቺ ጋር ተገበያዩ፤ብዙ የጠረፍ አገሮችም የንግድ ደንበኞችሽ ነበሩ፤ በዝኆን ጥርስና በዞጲ ሸቀጥሽን ይገዙ ነበር።