ሕዝቅኤል 27:29-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ቀዛፊዎች ሁሉ፣መርከባቸውን ጥለው ይሄዳሉ፤መርከብ ነጂዎችና መርከበኞችም ሁሉ፣ወርደው ባሕሩ ዳር ይቆማሉ፤

30. ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣በምሬት ያለቅሱልሻል፤በራሳቸውም ላይ ዐቧራ ነስንሰው፣በዐመድ ላይ ይንከባለላሉ።

31. ስለ አንቺ ጠጒራቸውን ይላጫሉ፤ማቅም ይለብሳሉ፤በነፍስ ምሬት፣በመራራም ሐዘን ያለቅሱልሻል።

ሕዝቅኤል 27