ሕዝቅኤል 27:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፤

3. በባሕር መግቢያ ላይ ለምትገኘውና በብዙ ጠረፎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ለጢሮስ እንዲህ በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጢሮስ ሆይ!፤“ፍጹም ውብ ነኝ” ብለሻል፤

4. ዳርቻሽ በባሕር መካከል ነው፤ሠሪዎችሽም ፍጹም ውብ አድርገውሻል።

ሕዝቅኤል 27