ሕዝቅኤል 26:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የጥንት ዘመን ሰዎች ወደ ገቡበት ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፤ ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር በጥንቱ ፍርስራሽ ከምድር በታች አኖርሻለሁ፤ ከዚህም በኋላ በሕያዋን ምድር ተመልሰሽ ቦታ አታገኚም፤

21. መጨረሻሽን አሳዛኝ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም፤ ትፈለጊያለሽ፤ ከቶም አትገኚም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ሕዝቅኤል 26