ሐዋርያት ሥራ 23:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ደብዳቤም ጻፈ፤ እንዲህ የሚል፦

26. ከቀላውዴዎስ ሉስዩስ፤ለክቡር አገረ ገዥ ለፊልክስ፤ሰላም ለአንተ ይሁን።

27. አይሁድ ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ነገር ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ፣ ከወታደሮቼ ጋር ደርሼ አተረፍሁት።

28. ለምን ሊከሱት እንደ ፈለጉ ለማወቅም፣ ወደ ሸንጎአቸው አቀረብሁት።

29. የተከሰሰውም ሕጋቸውን በተመለከተ እንጂ ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ።

ሐዋርያት ሥራ 23